Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dpr

Department of Parks and Recreation
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about Department of Parks and Recreation services for Amharic speakers.

የኤጀንሲው ስም፡   
የኮሎምብያ ዲስትሪክት የፓርክ እና የመዝናኛ መሥሪያ ቤት  
 

ተልዕኮ

የኮሎምብያ ዲስትሪክት የፓርክ እና የመዝናኛ መሥሪያ ቤት (DPR) ተልዕኮ የተለያዩ ፕሮግራሞችን፣ እንቅስቃሴዎንችን እና ዝግጅቶችን በማቀነባበር በሁሉም ዕድሜ ክልል ለሚገኙ የዲስትሪክቱ ኗሪዎች እና ጎብኝዎች ተመጣጣኝ እና ጥራት ያለው የመዝናኛ አገልግሎቶች በመስጠት የኑሮ ሁኔታን እና ጤንነትን ማጎልበት ነው። እንኝህን እንቅስቃሴዎች ለማካሄድ DPR 92 የመጫዎቻ ሜዳዎች፣ 68 የመዝናኛ ማዕከሎች፣ 900 ኤከር የመዝናኛ ሜዳዎች፣ 40 የውሀ መዝናኛዎች (የዋና እና ፏፏቴ ሜዳዎች)፣ 375 ሜዳዎች፣ ከ200 በላይ የቅርጫት ኳስ እና የቴኒስ ሜዳዎች እና ከ100 በላይ የሩጫ ሜዳዎች አሉት። ስለ DPR የበለጠ መረጃ ለማግኘት በ(202) 673-7647 ይደውሉ ወይም በኢ-ሜል [email protected]  ያግኙን።

የሚከተሉት በDPR የሚሰጡ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ናቸው።
 

  • የውሀ ስፖርቶች ክፍል በሁሉም ዕድሜ ክልል ለሆኑ እና የዋና ችሎታ ላላቸው ኗሪዎች እና ጎብኝዎች በርካታ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የውሀ ስፖርት ፕሮግራሞች እና ህንጻዎች በመላው በዲስትሪክቱ ያካሂዳል። የህንጻ ውስጥ መዋኛዎች ዓመቱን በሙሉ እና የውጭ መዋኛዎች እና የውሀ ርጭት ሜዳዎች በበጋ ወራቶች አገልግሎት ይሰጣሉ። 

  • የማህበረሰብ የአትክልት ክፍል በመላው በዲስትሪክቱ የአትክልት ቦታዎች ለማዘጋጀት ከህብረተስቡ ጋር ይሠራል።  በአሁኑ ጊዜ DPR በግዛቱ 13 የማህበረሰብ የአትክልት ቦታዎች አሉት።

  • የተለያዩ የህብረተሰብ ዕቅዶች ክፍል የተለያዩ ህብረተሰቦችን የተመለከቱ ፕሮጀክቶች እና ውጥኖችን በመጠቀም የባህል ብቁነቱን ያስፋፋል፣ እውነታዎችን እና መረጃዎችን ይሰጣል፣ እንዲሁም በዲስትሪክቱ ውስጥ በመበልጸግ እና በማደግ ስለሚገኘው ዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ግንዛቤ ይሰጣል።   

  • የታዳጊ ልጆች/ጊዜያዊ ፕሮግራሞች/የካምፖች ክፍል የፓርክና የመዝናኛ መሥሪያ ቤትን የበጋ፣ የክረምት እና የበልግ እረፍት ጊዜ ካምፖችን፣ የDPR የጨዋታ ቀን እና የፓርክና የመዝናኛ መሥሪያ ቤት ዕድሜያቸው ከ18 ወር እስከ 12 ዓመት ለሆናቸው ወጣት ኗሪዎች የቡድን ጨዋታ ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል።      

  • የአካባቢ እና ከቤት ውጭ ክፍል ስለተፈጥሮ የበለጠ ግንዛቤ እና ግንኙነት እንዲኖራቸው የትምህርት ፕሮግራሞች እና የውጭ የመዝናኛ ፕሮግራሞች በማዘጋጀት ከዲስትሪክቱ ኗሪዎች ጋር በትብብር ይሠራል።  

  • የአመጋገብ አገልግሎቶች ክፍል  በኮሎምብያ ዲስትሪክት አካባቢ በርካታ ነጻ የምግብ ፕሮግራሞችን በዲሲ የፓርክና መዝናኛ መሥሪያ ቤት ማዕከሎች ያካሂዳል።  ትምህርት ቤት በሚዘጋበት በበጋ ወቅት ዕድሜያቸው እስከ 18 ዓመት ለሆናቸው ልጆች የተመጣጠነ ነጻ ምግብ እና መክሰስ ያቀርባል።  
  • የባልደረቦች እና የበጎ ፈቃድ ሠራተኞች ክፍል በህብረተሰቡ በጎ ፈቃደኞች በከፊል የተደገፈ እና DPR ሁለገብ በሆኑት የዲስትሪክቱ አካባቢዎች እና ማህበረስቦች በሰፊው እንዲንቀሳቀስ በሚሠሩ ፕሮግራሞች የተደገፈ ነው።    

  • ፈቃድ እና ቦታ ማስያ ክፍል  ለአንዳንዶቹ የDPR ፓርክ እና የመዝናኛ ህንፃዎች፣ ፓርኮች፣ ሜዳዎች፣ የስፖርት መሥሪያ ቦታዎች እና ተንቀሳቃሽ መድረኮች ለተለያዩ የህዝብ ጥቅሞች እንዲውሉ ፈቃድ ይሰጣል።

  • የተዘዋዋሪ መሪዎች ፕሮግራም በጣም ጠቃሚ ነው።  ተዘዋዋሪ መሪዎች በወጣቶችና አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች መካከል የቅርብ ግንኙነት በመፍጠር ለወጣቶች እና ዕድሜያቸው በ8 እና በ24 ዓመት መካከል ለሆነ ወጣት ቡድኖች የጥላቻ ጠባዮችን ያስቆማሉ፣ ያገላሉ እና ይቆጣጠራሉ።

  • የአረጋውያን አገልግሎቶች ክፍል በዲስትሪክቱ በሚኖሩ አረጋውያን ላይ በማተኮር ለአረጋውያኖች ጠቃሚ እና አዝናኚ የሆኑ በእራስ መተማመን ላይ ያተኮሩ ዓመቱን በሙሉ የሚካሄዱ ፕሮግራሞች እና ልዩ ዝግጅቶች ያካሂዳል።

  • የስፖርት፣ የጤና እና የሰውነት ማጠናከሪያ ክፍል የተለያዩ ወቅታዊ የውድድር እና ውድድር የማያስፈልጋቸው ትምህርታዊ የስፖርት ፕሮግራሞች በሁሉም ዕድሜ ክልል እና ችሎታ ላላቸው ይሰጣል።  የተለያዩ የሰውነት ማጠናከሪያ ትምህርቶች፣ የእንቅሰቃሴ ስፖርት ዕድሎችን እና የአመጋገብ ትምህርት ፕሮግራሞችን በመላ ከተማው  በሚገኙ ስፍራዎች ይሰጣል።  

  • የወጣቶች ፕሮግራም ክፍል ዕድሜያቸው በ13 እና በ19 ዓመት መካከል ለሆነ ወጣቶች ዓመቱን በሙሉ በንቃት  በባህላዊ እና ማህበራዊ ኑሮ ልምድ እንዲሳተፉ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያካሂዳል።  

  • የፈውስ መዝናኛዎች ክፍል  የአሜሪካ የመፈወስ መዝናኛ ማህበር ከሚሰጣቸው ፕሮግራሞች ጋር ተመጣጣኝ የሆኑ የአካል ጉዳት ያለውን ሰው ተከታታይ በሆኑ ልዩ የፈውስ መዝናኛ ፕሮግራሞች አማካይነት የመሳተፍ ደረጃውን ወደነበረበት ለመመለስ፣ ለማጥፋት እና ለማገገም ፕሮግራሞችን ያክሂዳል።  

አድራሻ
የዲ.ሲ. የፓርክ እና የመዝናኛ መሥሪያ ቤት
1250 U St., NW, 2nd Floor
Washington, DC 20009
Phone: (202) 673-7647
Fax: (202) 673-2087
www.dpr.dc.gov

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/dcdpr 
ትዊተር: https://twitter.com/dcdpr